Mental Stress : ከአእምሮ ጭንቀት ራስን ለመጠበቅ የሚረዱን መንገዶች

 

🧠 የአእምሮ ጭንቀት 😨

Mental stress

🔅 የአእምሮ ጭንቀት ምንድነው?

የአእምሮ ጭንቀት ህመም ነው። ሰው፣ ደረጃ፣ ኃይማኖት፣ ጎሳ፣ ዘር፣ ቀለም፣ ፆታ  ሳይለይ የሚያጠቃ በሽታ ነው። ከሌላው በሽታ ለየት የሚያደርገው መድኃኒት እያለው የለለ መምሰሉ ነው።

የአእምሮ ጭንቀት የራስን ሚስኪንነትና ዋጋ ቢስነት አምኖ በመቀበል የሚመጣ የመንፈስ ጭንቀት ነው።

የሰውን የመኖር ፍላጎት ከሚያጨልሙ እንዲሁም ሚዛናዊ የሆነ ህይወት እንዳይኖረው ከሚያደርጉ ወይም አእምሮ ሙሉ በሙሉ እንድስት ከሚያደርጉ ልዩ ልዩ  ምክንያቶች የአእምሮ ጭንቀት የመጀመሪያውን ደረጃ ይይዛል።

የአእምሮ ጭንቀት የሰው ህይወትን ካለጊዜው ገርስሶ ከሚጥሉ ገፍታሪ ሃይሎች መካከል አንደኛው ነው። በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ የመጨረሻው የአእምሮ ጭንቀት ውጤት የራስን ህይወት በገዛ እጅ ማጥፋት ነው።

የአእምሮ ጭንቀት "ደስታ ገፋፊ" በመባልም ይታወቃል። አንድ ሰው በአእምሮ ጭንቀት ስያዝ ከዛ ሰው ጋ ደስታ ጨርሶ ይርቃል። ምክንያቱም የአእምሮ ጭንቀት ደስታን የመግፈፍ ሃይል አለው። በዚህም በቀላሉ ደስታውን ገፎ ያርቅበትና ደስታ አልባ ያደርገዋል።

💢 የአእምሮ ጭንቀት እንዴት ይከሰታል?

How mental stress occur

ሰዎች እንደጠበቁት የውድድሩ አሸናፊ ካልሆኑ፣ የወጠኑትና የተመኙትን ማግኘት ካልቻሉ ለአእምሮ ጭንቀት ይጋለጣሉ።

ራስህ ባዶ የሆንክ፣ ምንም  የማትረባና ፋይዳ የለለህ ከመሰለህ ጠርጥር ይሄ የአእምሮ ጭንቀት ውጤት ነው።

በተጨማሪም ለራስህ ዝቅተኛ አስተሳሰብ፣ ምንም መስራት የማትችል፣ ዋጋ የለለህ፣ ሁኔታዎች የጨለሙብህ፣ መንገዶች ሁሉ የተዘጉብህ መስሎ ሊሰማህ ይችላል። ይሄ የአእምሮ ጭንቀት ስሜት ነው።

የአእምሮ ጭንቀት ለራስ መጥፎ ግምትን በመስጠት ይፈጠራል። ለራስህ በጣም ዝቅ ያለ መጥፎ ግምት በተደጋጋሚ የሚትሰጥ ከሆኔ አንድ ቀን የአእምሮ ጭንቀት ሊከሰትብህ  እንደሚችል እወቅ።

የአእምሮ ጭንቀት ሰውን የሚይዘው መጀመሪያ ላይ በምክንያት ሆኔ ያለምክንያት ልቡ በትልቅ ሀዘን ወይም ትካዜ ሲሞላ ነው። ይሄ በውስጥህ  የተፈጠረው የሀዘን ስሜት ስር ሳይሰድ በወቅቱ አስወግደህ መጣል ካቃተህና በውስጥህ ከቆየ እንዲሁም በእለታዊ ኑሮህ ውስጥ ገብቶ እርሚጃህን  የሚያደናቅፍ ከሆኔ ሀዘኑ ተራ ሀዘን ወይም ትካዜ መሆኑ ይቀርና ወደ አእምሮ ጭንቀት ይለወጣል።

ስልቹ መሆን ወደ አእምሮ ጭንቀት ይመራል። ስልቹ ሰው እለታዊ ኑሮው ያልጣፈጠና የደበዘዘ ሆኖ ይሰማዋል። ብዙ ግዜ ስልችት ካለ ህይወት ውስጥ ቀስቅሶ የሚያስወጣውን ነገር ይፈልጋል። የሚያነቃቃውን ስራ ይፈልጋል። በሌላ አንፃር ደግሞ “ስራ በዛብኝ” ብሎ ስያማርር ይሰማል። በሚሰራው ስራ ጣእምና ትርጉም ያጣበታል። አልፎ አልፎ መጠኑ ይለያይ እንጂ ሁላችንም በኑሮአችንና በእለታዊ ስራችን ጣእም የሚናጣበትና ስልችት የሚለን ግዜ አለ። ከዚህ ስሜት ነፃ የሆኔ ሰው የለም። አንዳንድ ሰዎች ከዚህ ስልችት ከሚል ህይወት ነጻ ለመውጣት ስሉ በመጠጥ፣ በአደንዛዥ እፅ፣ በቴለቭዥን፣ በሲኒማና በመሰል ነገሮች ላይ ሰፊ ጊዜያቸውን ያሳልፋሉ። እንዲሁም ብዙ ገንዘባቸውን ያጠፋሉ። ይሄ ስሜት እየቀጠለና እያደገ ከሄደ ቀስ በቀስ ካሉበት ህብረተሰብና እውነት እየሸሹ እንዲሄዱ ስለሚያደርጋቸው የአእምሮ ጭንቀት ይደርስባቸዋል።

💢 የአእምሮ ጭንቀት መንስኤ

The cause of mental stress

ተስፋ መቁረጥ

➠ ተስፋ የለኝም ብሎ ማሰብ
➠ ከዚህ አልወጣም፣ መውጣት አልችልም፣ እድል የለኝም
➠ እኔ መዳን አልችም
➠ ሁኔታዎች በህይወቴ አይሻሻሉም

በማለት በር ዘግቶ፣ እራስን ደብቆ መኖር ነው ተስፋ መቁረጥ።
ይሄ ማንኛውንም ሰው ቢሆን ወደ ከፋ የአእምሮ ጭንቀት ውስጥ ይከታል እንጂ መፍትሔ አይሆንም። ተስፋ ሲመነምን ልብ በሀዘን ይደቃል፤ ልብ በሀዘን ስደቅ አእምሮ ጭንቀት ውስጥ ይገባል።

ማጣት

ማንኛውም ሰው በህይወቱ የሚገጥመውን፣ በቤተሰቡ የሚደርሰውን ሞት ወይም ሌላ አይነት ጉዳት መቋቋም ወይም መወጣት ስያቅተው የአእምሮ ጭንቀት ሊደርስበት ይችላል።

ይሄ ማጣት የምንለው ለምሳሌ

➠ የጋብቻ መፍረስ
➠የሚወዱትን በሞት ማጣት
➠ ከሥራ መሰናበት
➠ በሚወዱት ጓደኛ መከዳት
➠ የጋብቻ ቃል ኪዳን መፍረስ
➠ ከሹመት መሻር ወዘተን ያጠቃልላል።

ሀዘን

ሰው የሚደርስበትን ሀዘን በአግባቡ ካልተወጣ ሀዘኑ አይሎ ወደ አእምሮ ጭንቀት ይለወጣል።

ተጨማሪ መንስኤዎች፡

👉 በህይወት በጎ ያልሆኑ አንዳንድ ጥቃቅን ነገሮች ሲደርሱብን
👉 የሚንወደውና ይሆንልናል ብለን የጠበቅነውን ስናጣ
👉 ክብራችን [ego] የተነካ ስመስለን
👉 የተስፋ ቢስነት ስሜት
👉 ከመጠን ያለፈ ሀዘንና ትካዜ
👉 የባዶነት ስሜት
👉 ከመጠን ያለፈ የበደለኛነት ስሜትና የኃፍረት ስሜት
👉 ሰዎች እንደጠበቁት የውድድሩ አሸናፊ መሆን ካልቻሉ፣ የወጠኑትንና የተመኝትን ማግኘት ካልቻሉ ለአእምሮ ጭንቀት ይጋለጣሉ።

የአእምሮ ጭንቀት ራስን ባዶ፣ የማይረባ፣ ጥቅም የለለው አድርጎ ከማየት ይፈጠራል።
ለራስህ ዝቅተኛ አስተሳሰብ ካለህ፣ ምንም መስራት የማትችል፣ ዋጋ የለለህ፣ ሁኔታዎች የጨለሙብህ፣ መንገዶች የተዘጉብህ ስመስልህ  ያኔ በአእምሮ ጭንቀት ትያዛለህ።ሰው የህይወቱን አመራር ሌሎች ስወስኑለት፣ ሰዎች በፈለጉት አቅጣጫ ስሜቱን ስጋፉት እንዲሁም የራሱ የሆኔ ውሳኔና እርሚጃ እንደለለው ስመስለው ለአእምሮ ጭንቀት የተጋለጠ ይሆናል።

💢 የአእምሮ ጭንቀት እንዳይደርስብን አስቀድመን ለመከላከል

To prevent mental stress

➠ ጥሩ ልማድ ራስን ማለማመድ
➠ ሀዘንን በአግባቡ መወጣት
➠ ትክክለኛ አስተያየት ይኑረን
➠ ትክክለኛ ያልሆኔ ትርጉም ከመስጠት መጠንቀቅ
➠ በህይወታችን አብልጠን የሚናየው ምን እንደሆኔ እንወቅ
➠ የዋጋ ቢስነት ስሜት አይሰማን
➠ የሌሎች ስሜት የእኛን ስሜት አይቆጣጠር
➠ ትኩረት ማድረግን መለማመድ
➠ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማዘውተር
➠ የግል ንፅህናን መጠበቅ
➠ ትዕግስትንና ፅናትን ማዳበር
➠ ራስን ከሌላው ጋር አለማወዳደር

ማንኛውም ሰው ሊደርስበት ከሚችለው የአእምሮ ጭንቀት ሊያመልጥ የሚችለው በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ሀዘኑን በአግባቡ መወጣት ስችል ነው።

ሀዘንን በአግባቡ፣ በትክክል  በመወጣት የአእምሮ ጭንቀት እንዳይደርስብን መከላከል እንችላለን።

ሰው “ጉዳት ደረሰብኝ” ስል ጉዳቱ የሚለካው የጠፋበት ነገር ለሰውየው ባለው ጠቃሚነት ወይም ክብዴት ነው። የጠፋበት ነገር ወይም የጎደለበት ነገር ሰውየው በህይወቱ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው ከሆኔ ጉዳቱም በዚያው መጠን ከፍ ያለ ይሆናል። ማንኛውም ሰው በህይወቱ የሚያስቀድማቸው ወይም ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጣቸው የራሱ የሆኔ ነገሮች አሉት።

እነዚህ ሰው በህይወቱ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸው ነገሮች ምን እንደሆኑ ለይቶ ማወቅ የአእምሮ ጭንቀት እንዳይደርስብን የምንከላከልበት የመጀመሪያው እርሚጃ ነው።

የአእምሮ ጭንቀት እንዳይደርስብን ለመከላከል ቁርጥ ያለ ውሳኔና በአግባቡ መራመድ ያስፈልጋል።

በሚገጥመን መጥፎ ሁኔታዎች በመገልገል ወይም ለበጎነት እንድውል በማድረግ ራሳችንን ከአእምሮ ጭንቀት መከላከል እንችላለን።

ማንኛውም ሰው አቅሙን አውቆ በአቅሙ ልክ ብራመድ ራሱን ከአእምሮ ጭንቀት መከላከል ይችላል።

ሰውነታችን በቅ እረፍት እንዲያገኝ በማድረግ የአእምሮ ጭንቀትን መከላከል ይቻላል። ሰውነታችን ከሚገባው በላይ ሥራ እንድሰራ በማስገደድ የሚናተርፈው የአእምሮ ጭንቀት ብቻ ነው። ስለዚህ ለሰውነታችን በቂ የሆኔ እረፍትን በመስጠት ያንን ጭንቀት አስቀድመን መከላከል እንችላለን።

ለበለጠ መረጃና ለእርዳታ

telegram: @yonasgizawjb
Email: yonasgizawjb@gmail.com


Comments