The Hidden Truth About Money | የገንዘብ ምስጢር

hidden truth about money, money secrets, financial freedom, wealth mindset, investing for beginners, money management.

The Hidden Truth About Money | የገንዘብ

Introduction 

አለም ላይ ከህፃን እስከ አዋቂ ሁሉም አጥብቆ የሚፈልገው አንድ ነገር አለ። ሁሉም በየፊናው ያንን ነገር ለማግኘት ይሮጣል። ልክ ካለሱ ህይወት የለም እንደተባለ ሁሉም የህይወቱን መሠረት እሱ ላይ ጥሏል። ተማሪው ተምሮ፣ ሠራተኛውም ሰርቶ ማግኘት የሚፈልገው እሱን ነው። እንደ አለመታደል ሆኖ ፈላጊው ብዙ ሚያገኘው ግን ጥቅቱ ነው።

ይገርምሃል አንተም ራሱ እጅህ ሊታስገባው ብዙ ግዜ ደክመሃል። ይህንን የሚታነበው እንኳን የእሱ ስም ስላለበት ነው። 

ገንዘብ 

ገንዘብ ምንድንነው?

እርግጥ ነው ገንዘብ የተሰራው ልክ እንደ ጋዜጣ ከተራ ወረቀት አይደለም። ቢሆንም ግን ወረቀት ነው። ገንዘብ ምንም ያህል ብከመር በአንድ ክብሪት ይቃጠላል። ወረቀትም አይደል።

ታድያ ይሄ ተራ ወረቀት እንዴት ኃይል ያለው ነገር ሆነ?

ነገሩ ወዲህ ነው የሰው ልጅ "ጥረህ ግረህ ብላ" ተብሎ ከተፈረደበት በኋላ የላቡን ለመብላት ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም። አንዱ እንሰሳ ስያረባ ሌላው ጥራጥሬ ዘራ። ታድያ አንዱ የሌላውን ምርት ለመቀበል ስል "ግብይት" የተባለን ቴክኖሎጂ ፈጠረ። ይህንን ግብይት ለማስከድ በሚደረግ ልውውጥ ነው እንግዲህ በሰባተኛው ክፍለ ዘመን ቻይናውያኖች የወረቀት ገንዘብን የፈጠሩት።

ገንዘብ ተራ ቁስ ከሆኔ ኃይሉ ከየት መጣ?

ዶላር፣ ፓውንድ፣ ዩሮ፣ ብር ሁሉም ወረቀት ናቸው። ነገር ግን እጅግ ሃይለኛ ኃይል አላቸው። ገንዘብ ተራ ቁስ ነው ነገር ግን የማይገዛው  ነገር የለም። ገንዘብ ተራ ወረቀት ነው ነገር ግን የማያደርገው ነገር የለም። 

እንዴት?

የገንዘብ ኃይል 

በእውነቱ ገንዘብ ይሄን ያህል ኃይል ያለው ነገር ሆኖ አይደለም። ገንዘብ ተራ ቁስ፣ ተራ ወረቀት ነው። ያ ኃይል የተፈጠረው በሰዎች አስተሳሰብ ነው። እስቲ ሰው የሌለበት ጫካ ወይም ምድረበዳ የሚሊዮን ዶላር ካሽ ቢኖርህ ምን ታደርጋለህ?

አየህ! ሰው ከለለ ገንዘብም ኃይል አይኖረውም። ገንዘብ ሁለት ሰዎች ተባብረው ለወረቀት የሰጡት የኃይል አስተሳሰብ ነው። ሰዎች እስካሉ ድረስ ኃይሉ ስሰራ ይኖራል።

ከህይወትህ ገንዘብን አብልጠህ ካየህ ምናልባት ለገንዘብ ስትል የሰው ህይወት ሁላ ሊታጠፋ ትችላለህ። ያንን ገንዘብ ተሸክመህ ምድረበዳ ብትሄድ ገንዘብ ተራ ወረቀት እንደሆነ ይገባሃል።

ገንዘብ ኃይል የሚኖረው በአንተ አስተሳሰብ ልክ ነው። ከምንም ገንዘብን አብልጠህ ካየህ ገንዘብ ከምንም በላይ ኃይል ያለው ነገር ይሆንብሃል። ለብዙዎችም የሆነው ይሄው ነው።

ታድያ ገንዘብን እንዴት ማየት ነበረብን?

ገንዘብ ተራ ቁስ ነው ተራ ወረቀት። ምንም እንኳን በሃሳባችን የሰጠነው ኃይል ቢኖረውም የእኛ ጌታ ሳይሆን የእኛ ባሪያ ነው።

ገንዘብን ከምንም አብልጠው የተመለከቱት ለገንዘብ ኃይል ተገዝተው ባሪያዎች ሆነው ይኖራሉ። ወር የሚጠብቁ ለማኞች።

በእውነቱ ገንዘብ የእኛ ሠራተኛ እንጂ እኛ የገንዘብ ባሪያዎች አይደለንም። ለገንዘብ እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ከለለን ገንዘብ ባይኖረን ይመረጣል።

ቢሊገትስ፣ ባፌት፣ ኤሎን ማስክና መሰሎቹ ገንዘብን ባሪያቸው አድርገው የሚያሰሩት ገንዘብን አገልጋያቸው አድርገው ስለሚያስቡ ነው። 

እውነት ነው ገንዘብ የሚትፈልገውን አድርጎ እንዲያገለግልህ ነው የተፈጠረው። ታድያ ለምን ለገንዘብ ባሪያ ሆነን እንኖራለን?

ዛሬውኑ አስተሳሰብህን ለውጥ!

ገንዘብ እጅህ ስገባ ምን አድርገ አመጣው ብለህ ሳይሆን ምን ሊያደርግልኝ መጣ ብለህ ማሰብ ጀምር። እጅህ የገባው ገንዘብ አንተን የማያገለግል ሌላ ገንዘብ የማያመጣ ከሆነ እጅህ ባይገባ ይመረጣል።


hidden truth about money, money secrets, financial freedom, wealth mindset, investing for beginners, money management.

#MoneySecrets #FinancialFreedom #WealthMindset #HiddenTruth #MoneyTips

Comments