👀 እይታ 👀
ሁለቱም ሰዎች ወደተላኩበት ሀገር ስደርሱ የሄዱበት ሀገር ሰዎች አይደለም ጫማ ሊያደርጉ ይቅርና እግራቸው እስኪሰነጠቅ ድረስ በባዶ እግር የሚሄዱ ስለ ጫማ በጭራሽ የማያውቁ ነበሩ።
አንደኛው ሰው “እንዴ! ምን አይነት ሀገር ነው የላካችሁኝ…እዚህ ሰዎች ጫማ ልገዙ ይቅርና ጫማ ምን እንደሆኔ እንኳን አያውቁምኮ። በሉ በፍጥነት ወደ ቤቴ መልሱኝ“ ብሎ ወደ ድርጅቱ ደብዳቤ ይፅፋል። ድርጅቱም ያ ሰው እንድመለስ አደረገው። ሰውየውም ባዶ እጁን ወደ ቤቱ ተመለሰ።
ሁለተኛው ሰው ግን ለድርጅቱ ”ዋው! በጣም ትክክለኛ ቦታ ነው የላካችሁኝ። እዚህ ህዝቡ በጫማ እጦት እግሩን እየጨረሰ ነው። አሁኑኑ አምስት ኮንቴነር ጫማ ላኩልኝ“ ብሎ ደብዳቤ ፃፈ። ድርጅቱም እንዳለው አምስት ኮንቴነር ጫማ ላከለት። ያም ሰው ለዛ ሀገር ሰዎች ስለጫማ እያስተማረ ጫማ መቸብቸብ ጀመረ። ምን ያ ብቻ በድጋሚ ሌላ ተጨማሪ አምስት ኮንቴነር ጫማ አስልኮ መሸጥ ጀመረ። ያ ሰው ከጫማ ሽያጭ በርካታ ኮምሽን አገኘ ድርጅቱንም ትርፋማ አደረገ።
የሁለቱ ሰዎች ልዩነት እይታ ነበረ። የመጀመሪያው ሰው የነበረው እይታ መጥፎ እይታ ነበረ። ምክንያቱም ነገሮችን በመጥፎ ጎኑ ነበረ ያየው። በዚህም የመጣለትን ጥሩ እድል ሳይጠቀምበት ባዶ እጁን ወደመጣበት ተመለሰ። ሁለተኛው ሰው ግን የሚገርም ጥሩ እይታ ነበረው። ነገሮችን ከጥሩ አንግል ነበረ የተመለከተው በዚህም ራሱንና ድርጅቱን ልጠቅም ችሏል።
እይታህ ሳይቀየር ሃሳብህን ብትቀያይር ዋጋ የለውም። የሁሉ ነገር መሰረት ሀሳብ ነው። የሀሳብ መሰረቱ ደግሞ እይታ ነው። ስለዚህ ራስህን መቀየር ካለብህ በመጀመሪያ ቀድመህ እይታህን ነው መቀየር ያለብህ።
የሰው ልጅ ሁለቱ እይታ
የሰው ልጅ ነገሮችን በሁለት ጎን ሊያይ ይችላል።
➠ በጥሩ ጎን
➠ በመጥፎ ጎን
🔅 ጥሩ ጎን
የነገሮች ጥሩ ጎን የነገሮች መልካሙ ክፍል [side] ነው። ነገሮችን በመልካም ጎናቸው፣ ደስ በሚያሰኘው ጎናቸው ስንመለከት ያኔ እይታችን በጥሩ ጎን ሆኔ ወይም ጥሩ እይታ አየህ ይባላል።
🔅 መጥፎ ጎን
የነገሮች መጥፎ ጎን የነገሮች መጥፎው ክፍል [side] ነው። ነገሮችን በመጥፎ ጎናቸው [angle]፣ ደስ በማያሰኘው ጎናቸው ስንመለከት ያኔ እይታችን በመጥፎ ጎን ሆኔ ወይም በመጥፎ እይታ አየን ይባላል።
አንዳንድ ሰዎች ምንም ነገር ስገጥማቸው የሚገጥማቸውን ነገሮች በመጥፎ ጎኑ [angle] ብቻ ያያሉ። ይሄ እይታቸው ለሚገጥማቸው ነገሮች መጥፎ አመለካከት እንድኖራቸው ያደርጋቸዋል። መጥፎ አመለካት ደግሞ መጥፎ አስተሳሰብን ይፈጥራል።
እንደሚታወቀው ሀሳብ ስደጋገም በጥልቁ አእምሮ እምነትን ይዞ ይወቀራል። መጥፎ አስተሳሰብም ስደጋገም በጥልቁ አእምሮ እምነትን ይዞ ይወቀራል። ከዛ ጥልቁ አእምሯችን ፈለግነውም አልፈለግነውም ያንን እምነት ወደ ድርጊት ይቀይረዋል። የዛኔ መጥፎ ድርጊቶችን እንድታደርግ ትገፋፋለህ። መጥፎ ድርጊቶች ደግሞ መጥፎ ውጤትን ከመስጠት ወደ ኋላ አይሉም።
ኒክ እጅና እግር ሳይኖረው ነው የተወለደው። ልክ እንደ ሌላው እግር እንዳለው ሰው መራመድ፣ መሮጥ ይፈልግ ይሆናል ግን አይችልም። ሙሉ እጅ እንዳለው ሰው ያሻውን መስራት ይፈልግ ይሆናል ግን አይችልም። ይሄ ነገር ብቻ ኒክ ነገሮችን በመጥፎ ጎኑ [angle] እንዳያቸውና እንድያማርር ከበቅም በላይ ነበሩ። ኒክ ግን አላደረገውም። ከመጥፎ እይታ ይልቅ ጥሩ እይታን መረጠ። በጣም የሚገርመኝ አካል ጎዶሎ ሆኖ መፈጠሩን እንደ እድል ያየበት እይታ ነው።
ኒክ “ምን አለ ካለ እጅና እግር ከሚፈጠር የእናቴ ሆድ ውስጥ ውሃ ሆኜ በቀረሁ” አላለም። ይልቁን “ድንቅና ልዩ ሆኜ ተፈጥሪያለሁ” ነበረ ያለው። ያ ጥሩ እይታ የኒክን ህይወት አቅልሎለታል። ስኬታማ ደራሲና ምርጥ የአነቃቅ ንግግር ተናጋሪ አድርጎታል።
አያድርሰውና በኤች አይ ቪ ቫይረስ ብትጠቃ “ሰዎች አውቀውብኝ ከሚያገሉኝ” ብለህ ዝም ብለህ ብትሞት ነው ወይስ በበሽታ መለከፍህን አውቀህና አሳውቀህ መድሃኒት እየተጠቀምክ በጥንቃቄ መኖርን ነው የሚትመርጠው? አየህ! እዚህ ጋ እይታ ጉልህ ሚና ይጫወታል።
ጥሩ እይታ የለለው ሰው በእርግጠኛነት የመጀመሪያውን ምርጫ ይመርጣል። ጥሩ እይታ ያለው ግን ነገሮችን በጥሩ ጎኑ ስለሚመለከት ጥሩ የሆነውን ሁለተኛውን ምርጫ ይመርጣል።
ከዚህ በፊት የነበረህን ውጤት የሰጠህ የገዛ ምርጫህ ነው። ለነገሮች የነበረህ እይታ ነው ውጤትህን የወሰነው። በዚህም ሱሰኛ ሆኔህ ይሆናል። ከስረህም ይሆናል። አየህ! እይታህ አመለካከትህን ፈጠረ። አመለካከትህም አስተሳሰብህን ፈጠረ። አስተሳሰብህ ስደጋገም በጥልቁ አእምሮህ እምነት ሆኖ ተገነባ። ጥልቁ አእምሮህ ደግሞ ወደድክም ጠላህም በአእምሮህ የተወቀረውን እምነት ወደ ድርጊት እንድትለውጠው አደረገህ። ድርጊትህ አሁን ያለህን ውጤት ሰጠህ። ይሄው ነው።
አሁን ያለህን የማትፈልገውን ውጤት መቀየር ከፈለክ መጀመር ያለብህ ከእይታህ ነው። ምክንያቱም ከዚህ በፊት የነበረህ ውጤት ጅማሮው ከእይታ ነበረ። ውጤትህን መቀየር ከፈለክ እይታህን መቀየር አለብህ። በፊት ነገሮችን በማይቻሉበት ጎናቸው የሚታይ ከነበረ አሁን ነገሮችን በሚቻሉበትና በሚሆኑበት ጎን ተመልከት።
አስታውስ! እይታህ ስቀየር አመለካከትህም ይቀየራል። አመለካከትህ ስቀየር በንቁ አእምሮህ የሚታስበው አስተሳሰብህ ይቀየራል። በንቁ አእምሮህ በተደጋጋሚ የሚታስበው አስተሳሰብ ስቀየር በጥልቁ አእምሮህ የተወቀረውም እምነትህ ይቀየራል። በጥልቁ አእምሮህ የተወቀረው እምነትህ ስቀየር ድርጊትህም ይቀየራል። ድርጊትህ ስቀየር ውጤትህም ይቀየራል።
እንግዲህ ለውጥ መጀመር ያለብህ ከእይታህ ነው። ምክንያቱም እይታህ የሁሉ ነገርህ መሰረት ነው።
ወዳጄ! እንደዚህ አይነት ስልጠናዎችን መውሰድ ከፈለክ

Comments
Post a Comment